Loading...
MOH eLibrary → Access to wealth of resources, research and publications!
Public Health Policy Policy

Health Policy Of The Federal Democratic Republic Of Ethiopia

4.0/5 (1 ratings)
2 likes
764 Downloads

Publish Date: August 2024

Document Description

ሀገራችን ልማትን ለማሳለጥና ከድህነት ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ እውን ለማድረግ የሰብዓዊ ልማት ለማህበራዊና ኢኮኖሚው እድገት አስተዋፆ ለማድረግ አሁን በስራ ላይ ያለውን የጤና ፖሊሲ ጨምሮ ሶስት ፖሊሲዎችን በማውጣት ስትተገብር ቆይታለች። በአገራችን የጤና ፖሊሲ ታሪክ የመጀመሪያው የጤና ፖሊሲ የተቀረጸው በ1960ዎቹ ሲሆን፤ ካስገኛቸው ስኬቶች መካከል ለብዙ ሰዎች ህመምና ሞት ምክንያት ከሆኑት ተላላፊ በሽታዎች መካከል ሀገራችንን ጨምሮ በዓለም ዓቀፍ ዘመቻ ፈንጣጣን ማጥፋት መቻሉ እና ወባን ለማጥፋት በተደረገዉ ጥረት በወረርሽኝ ይሞት የነበረውን ሰው ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉ ተጠቃሽ ናቸው። ሁለተኛው የጤና ፖሊሲ በ1970ዎቹ አጋማሽ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ የተጀመረበት እና የክትባት መርሃ-ግብር የተስፋፋበት ጊዜ ነበር። በ1986 ዓ.ም. የወጣውና እስከ አሁን እየተሰራበት ያለው ሶስተኛው የጤና ፖሊሲ የአገሪቱን ነባራዊ የጤና ችግሮች ባህሪይ፣ ስፋትና መሠረታዊ መንስኤዎችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ስለነበረ ለአገራችን ፈር ቀዳጅ የሆነው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ጨምሮ በሽታ መከላከል ላይ ያተኮረ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በስፋት የተሰራበት የጤና ስርዓት በመዘርጋት በተላላፊ በሽታዎች የሚመጣውን ሞትና ስቃይ ለመቀነስ እና የእናቶችና ህፃናት ጤና ማሻሻል አስችሏል። የሀገራችን ሕዝብ አማካኝ የመኖር ዕድሜ በ1987 ዓ.ም 49 ዓመት የነበረ ሲሆን በ2015 ዓ.ም 66.7 ዓመት መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የጤና ዘርፍ አገልግሎት ከተደራሽነት አንፃር መልካም ቢሆንም ጥራት እና ፍትሀዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አኳያ አሁንም ተግዳሮቶች አሉበት። አሁን ካለው ስነ-ህዝብ እድገት እና ስብጥር አንፃር፤ ከነባርና አዳዲስ በሽታዎች ስርጭት፤ እንዲሁም እየተፈጠሩ ካሉት የማህበራዊ ለውጥና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ደረጃ ጋር ተያይዞ እያደገ ከመጣው የሕዝብ ጤና አገልግሎት ፍላጎት ጋር አለመጣጣም ችግሮች ታይቷል። ከዚህ በተጨማሪ የላቀ ወይም የከፍተኛ ደረጃ የህክምና አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ ዜጎች ለከፍተኛ የህክምና ወጭ የሚዳረጉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ስለሆነም እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች እና እጥረቶችን ለመቅረፍ፥ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራት እና ፍትሐዊነት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማሻሻል፣ አለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ለውጦችን እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ ፖሊሲውን መከለስ አስፈልጓል። ይህ ፖሊሲ የጤና ዘርፍ ያለበትን ደረጃ በመገምገም የዘርፉን ዋና ዋና ችግሮችና የፖሊሲ ማነቆዎች በፖሊሲው የሚፈቱበትን አግባብና የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲው ተፈጻሚ ሲሆን የሚጠበቁ ቁልፍ ውጤቶችን በሚያሳይ መልክ ተዘጋጅቷል።







More Documents Like This



Top